CDMU የሦስተኛ ዙር የሰርትፊኬት ፕሮግራም ተማሪዎችን አስመረቀ

  • 24 March, 2026
News

በChrist Disciples Family ሀገር አቀፍ የጸሎት ፕሮግራም ላይ  በቀን 26/04/2018 ዓም በክራይስት ዲሳይፕልስ ጎስፕል ሚኒስትሪ ስር ሆኖ ትውልድን በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የሚያስታጥቀው ክራይስት ዲሳይፕልስ ሚሽን ዩኒቨርሲቲ የሦስተኛ ዙር የሰርትፊኬት ፕሮግራም ተማሪዎችን አስመርቋል።

ክራይስት ዲሳይፕልስ ሚሽን ዩኒቨርሲቲ በሰርትፊኬት  ፕሮግራም በኦንላይን ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ከጀመረ ወደ ዘጠኝ ወራት የሚጠጋ ጊዜ ሆኗል። በሰርትፊኬት ፕሮግራም ለክርስትና እምነት መሠረታዊ እንደሆኑ ያመንባቸውን ስድስት ትምህርቶችን እናስተምራለን። ትምህርቶቹ ነገረ ድነት፤ ደቀ መዝሙርነት፤ ትምህርተ ስላሴ፣ መጽሐፍ ቅዱስ እና የአጠናን ዘዴው፣ የነገረ ፍጻሜ መሠረታዊያን እና ሚሽን እና የወንጌል ሥርጭትን ያጠቃልላል። በ2017 ዓ.ም በሰርትፊኬት ፕሮግራም ተምረው የጨረሱ በመጀመሪያ ዙር 48 ተማሪዎችን እንዲሁም በሁለተኛው ዙር 17 ተማሪዎችን   በሁለት ዙር በአጠቃላይ 65 ተማሪዎችን Certify ማድረጋችን ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ በቀን 26/04/2018 ዓም በሰርትፊኬት ፕሮግራም ተምረው የጨረሱ 23 ተማሪዎችን Certify አድርገናል። ስለ ሁሉ እግዚአብሔር ክብሩን ይውሰድ።

የCD Mission University መሪ ቃል "ለሕይወት እና ለፍሬያማነት እንማር " "Study for life and Fruitfulness" ከመሆኑ አንፃር በዩኒቨርሲቲው  የሚማሩ ክርስቲያን ተማሪዎች የሕይወት ለውጥን በማስቀደም እንዲማሩ ትኩረታችን ነው። የዩኒቨርሲቲው መሪዎች "ዛሬ የምትመረቁ ተማሪዎቻችንም የሕይወት ለውጥን በማስቀደም ብዙ ፍሬ ለማፍራት በጸጋው እንድትተጉ በጌታ ፍቅር ማሳሰብ እንወዳለን።" የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።